የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሉት የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የተቀቀለ የእንጨት ምሰሶ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የማቀፍ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት |
የዕቃው ዝርዝር |
የጨረታው ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ
|
የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
1 |
የተቀቀለ የኤሌክትሪክ እንጨት ምሰሶ ከ8-10 ሜትር |
5,000.00
|
ሰኔ 15/2012 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 9:00 ሰዓት ላይ |
ሰኔ 15/2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 9፡30 ሰዓት
|
- በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የተቀቀለ የኤሌክትሪክ እንጨት ምሰሶ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የማቀፍ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ የዘርፉን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፍቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉበግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አንደኛ ፎቅ ፕሮክሩመንት፡ ሎጅስቲክስ ዌር ሃውስ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 101-1 በመምጣት የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡– ጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 101-1፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ፋይናንሻል ከቴክኒካል ኢቫሉዌሽን በኋላ የሚከፈት ሲሆን “ኦሪጅናልና ኮፒ” በማለየት በተለያየ ፖስታበማሸግ እና ሦስቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥርEEU-GAM/ REG-002/2012 የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 047-551-13 99” መደወል ይችላሉ፡፡
- የኤክትሪክ አገልግሎቱ የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት