የጨረታ ማስታወቂያ
ክልል ትም/ቢሮ በዩኒሴፍ በጀት ድጋፍ በ2013 ዓ.ም ከ6-7 ዓመት ዕድሜ የሞላቸው ሕፃናት ከቤተሰቦቻቸው ሳይርቁ በየሰፈሮቻቸው መማር እንዲችሉ
- የጽህፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
- የምዝገባ ሠርተፊኬት፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ተመዝገቢ የሆነ፡፡
- 2013 ዓ.ም ውዝፍ ግብር ነፃ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት / ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር / በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 19 በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 1% ሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን የሚያከናወኑበት ዋጋ ዋናውንና ኮፒ ሁለት [2] ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00-3፡30 ሰዓት ድረሰ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ አስገብቶ በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 047 551 01 36/ 047551
የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ትምህርት ቢሮ