ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለጉና በጌምድር ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2. የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር በላይ ከሆነ /የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 31 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 20/ሃያ ብር ብቻ / በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ቢሆንም ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈት ሂደቱ ላይ ቢገኙም ባይገኙም ከመክፈት አያግድም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሪ ገንዘብ ከሆነ በመመሪያው የገቢ ደረሰኝ በመሂ -1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ኦሪጅናል /ዋና/ በታሸገ ፖስታ ጉ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን የገዙትን የጨረታ ሰነድ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በተቀመጠው ሳፕል መሰረት እቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም በወጡት ጨረታዎች የጥራት ማረጋገጫ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከውል ሰጭ መ/ቤቱ ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ 1ዐ ፐርሰንት በማስያዝ ውል መውሰድ ያለብዎት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ውል ካልወሰደ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ በፍሉድ የተነካካና ስርዝ ድልዝ ከሆነ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፍኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨሬታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የባዕል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡
- ጨረታ አሸናፊው የሚለየው በጥቅል በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል፡፡
- እቃው የሚቀርበው ጉና በጌምድር ወረዳ ክምር ድንጋይ ከተማ በፑል ንብረት ክፍል ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ድርጅቱ ወይም አቅራቢው ማሸነፉ ተገልፆለት ለሚያቀርባቸው እቃዎች በጥራትም ሆነ በመጠን የተጠየቀውን እቃ ለማቀረብ ፍቃደኛ ያልሆነ እና ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ በግዥ መመሪያ 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
- ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0582510226 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የጉና
በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት