ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ መ/ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት
- የጽህፈት መሳሪያና የቢሮ አላቂ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ 5000/አምስት ሺ ብር/ በባንክ የተመሰከረ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሰነዱን ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ(ፖስታ) ሙሉ አድራሻቸውንና የፕሮጀከቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ እንዲሁም የማይነበብ ነጠላ ዋጋ የቀረበ ከሆነ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮለ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 50 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋቸውን ሞልተው የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም አድርጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነድማስገባት ይቻላል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል ፡፡ 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታውን ሂደት ተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
ለበለጠ መረጃ 0462720268/0913921119 ደውሉ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በወላይታ
ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር
ፋይ/ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት