የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ጉ/ሜ/ጤ/ጣ/01/2013
በጉ/ክ/ከ/ወ/04 ጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2013 ዓ/ም የበጀት ዓመት የተለያዩ
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ ጨርቅና ጫማዎች ፣
- የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት የሚሰጡ፣
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የእጅ መሳርያዎች፣
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፣
- የሻይ /ቡና / ለስላሳ መስተንግዶ፣
- የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከሪካሪዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡
- ከሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብ ሳይት/ የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ
- ሎት1፣2 ብር 3000.00
- ሎት3፣ ብር 2000.00 ብር
- ሎት 4፣5 ብር 1500.00
- ሎት 6፣7፣8፣9 ብር 1000.00 በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን CPO ዋናውን ወይም ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
- ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል 1ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 401 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በአንድ ወጥ በታሸገ ፖስታ /ኦርጅናልና ኮፒ/ ብቻ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀመ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
- የጨረታው ሣጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን በ10፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጽዳት እቃዎች፣ የጽህፈት መሣሪያዎችና የደንብ ልብስ ጥራት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በሚገኘው ግዥ ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ/ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፣
- መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ 20% /ሃያ%/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፣
- የጨረታው መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ፡– ቀጨኔ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ጀርባ ወ/4/ወጣት ማእከል ሆሊሲቪየር ት/ቤት አጠገብ 50 ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-0118- 29-98-37/ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር
ጉቶ ሜዳ ጤና ጣቢያ