የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4/2013
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የወልቂጤ ስቴድየም ትሪቡን ግንባታ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠየቁ፡-
- ደረጃቸው ሲሲ/ጂሲ 5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የዘመኑን የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴከኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡-
- ሀ/ ለቴከኒካል ዶከመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦሪጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ /ቴከኒካል በሚል በመለየት
- ለ/ ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ/ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፤
7. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል መምሪያ ስም መሰራት አለበት፤
8. ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል፤
9. የጨረታው ቴከኒካል ዶከመንት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
10.የፋይናንሺያል የፕሮጀክቱ ግንባታ ዋጋ ከቴከኒክ ግምገማ ውጤት በኋላ የቴከኒክ ግምገማውን ያለፉት ተጫራቶች ሰነድ ብቻ የጨረታው ኮሚቴው በማስታወቂያ በሚገልፀው ቀን ይከፈታል፤
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
- በአፈፃፀም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ዞኑ በሚከታተላቸው ፕሮጀክት ከሁለት በላይ ፕሮጀክት ያላቸው መወዳደር አይችሉም፡፡
ለበለጠ መረጃ 0113300112 የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ወልቂጤ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ