የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሸን ጅጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባድ የተያዙ የተለያዩ
- ኤሌከትሮኒክስ፣
- የቤት ማስዋቢያ፣
- አልባሳት፣
- የቤት ዕቃ፣
- ስፔርፓርቶች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በ2/2/2013 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች ሰማማላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፣ በጌታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቶች፡
- በዘርፍ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፡፡
- በጨረታው 100,000 (መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ የሚችል፡፡
- ተጫራቹ ለየአንዳንዱ ዕቃዎች የሚገዛበትን በመነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል:
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በአምስት ቀን የሚረከብ መሆን አለበት፡፡
- ዕቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በአምስት ቀን ወስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ያላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና መ/ቤቱ ተቀባይነት ካገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል::
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃዎቹን ካሸነፉ በኋላ ከጅጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ከፈለጉ እንደ ቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡
- ተጫራቹ የተለያዩ እቃዎችን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው በ6/2/2013 ከጠዋቱ 3፡00 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ በኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል::
- NB) አሽናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የሚከፍል መሆኑ ይታውቅ።
- 2. የ2012 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናስታውቃን ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅጅጋ ቅ/ጽ/ቤት