ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በጅማ ዞን የጉማይ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት
- የጽሕፈት መሳሪያ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም
- የጽዳት መሳሪያዎችን፣
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን እና
- ጥገና እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርቶች፡-
- 1ኛ. የ2012 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፤
- 2ኛ. በዘርፉ የ2013 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- 3ኛ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፣
- 4ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የመጨረሻውን ወር (VAT) ያወራረደበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- 5ኛ የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚችል፤
- 6ኛ የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከጉ/ወ/ፋ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሙግዛት የሚችል፤
- 7ኛ ተወዳዳሪዎች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ( ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት የሚችል፤
- 8ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻውን እና የድርጅቱን ስም እና ማህተም በመጥቀስ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 4/13/2012 ዓ.ም 6:00 ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- 9ኛ. ጨረታው በተባለበት ቀን እና ሰዓት ገብቶ ካለቀ በኋላ በ4/13/2012 ዓ.ም 6:30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8:00 ሰዓት በጉ/ወ/ፋ/ኢ/ት/ጽ/ቤት እንደሚከፈት ፤
- 10ኛ. አሸናፊ ተጫራቶች ከጽህፈት ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የውል ማስከበሪያ/ዋስትና/ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው።
- 11ኛ እዚህ ማስታወቂያ ላይ ያልተጠቀሱ መስፈርቶችን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ።
ማሳሰቢያ፡-
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-047-540-02-68 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በጅማ ዞን
የጉማይ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት