የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2013
- ሎት 1 የፅ/ት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2 የፅዳትና ተዛማጀ ዕቃዎች፣
- ሎት 3 ኤሌክትሪክና ተዛማጅ ዕቃዎች
- ሎት 4. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ ዕቃዎች፣
- ሎት 5 የህንፃ መሳሪያ እና የቧንቧ እቃዎች፣
- ሎት 6 የመኪና ዕቃዎች፣
- ሎት 7 የደንብ ልብስና ስፌት ዋጋ፣
- ሎት 8 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት 9 የህትመት ውጤቶች፣
- ሎት 10 የቤተ -ሙከራ እና ቤተ መዘክር ዕቃዎች፣
- ሎት 11 ኮምፒውተር ፣ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ስካነር፣ ጥገና እና ሰርቪስ
- ሎት 12 የመስተንግዶ ዕቃዎች፣
- በጨረታው ለመካፈል የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቀድና በፌደራል ግዥ ንብረት አስተዳደር ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፥
- ለጨረታ ማስከበሪያ (Bid BoNd ) በየሎቱ ብር 2000.00 /ሁለት ሺ ብር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያያዘውማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ በየሎቱ የተጠመሩትን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቀደም ሲል ባቀረበበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሲያስገቡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስሌት ሲሰላ ስህተት ቢኖረው መ/ቤቱ የሚወስደው ነጠላ ዋጋውን ይሆናል፡፡
- ተጫራቶች ለመወዳደር የሚያስገቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን መታወቅ ይኖርበታል፤ አጭር ጊዜ መስጠት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ በሰነዱ ላይ ተፈርሞበት እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ ፋይናንሻል እና ቴከኒካል ኦርጂናልና ኮፒ በማዘጋጀት ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% / አሥር በመቶ/ (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሲያቀርበ በሰነዱ ላይ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማኅተም ተደርጎበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አሥር/ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፣30 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ሆኖም የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- 14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አደራሻ፡- ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ጉለሌ ከከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል አለፍ ብሎ አጣሪ ሰፈር የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ህንፃ ቁጥር 2 2ኛ ፎቅ ላይ ስልከ ቁጥር-0118278471
የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል