የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በአንደኛው ዙር በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
- ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 3. የህትመት ውጤቶች፤
- ሎት 4 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 5- ልዩ ልዩ የቢሮ እቃዎች፤
- ሎት 6- የመኪና ግብዓቶች ፤
- ሎት 7- የፕሪንተር እና የፕላንት ማሽነሪ ጥገና እድሳት፤
- ሎት 8. የፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎች ጥገና እድሳት፣
- ሎት 9 የኤሌክትሪክ ጥገና፣
- ሎት 10- የጀነሬተር ጥገና፤
- ሎት 11- የፕላንት ማሽነሪ እና ቋሚ የዓይቲ እቃዎች ግዥ፣
- ሎት 12- የህንጻ ቁሳቁስ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥ በብሄራዊ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2013 ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፤
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር (online) የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የ2012 የታደሰ ንግድ ፍቃድና የምስክር ወረቀት ማቅርብ ይኖርበታል ፤
- 6 ወር ያላለፈው የጨረታ መወዳደሪያ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ ለየትኛው እቃ እንደሚወዳደሩ ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፤ በመስሪያ ቤቱ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ብቻ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ያስገቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን አለበት፣ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ሳሬም ሆቴል ከፍ ብሎ ሰሜን ማዘጋጃ በኤስኤም ኤስኤስ ህንጻ ላይ ግዥና ፋይናንስ የስራሂደት ቢሮቁጥር 407 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ለዚህ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል::
- የጨረታውን የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል ዶክመንት እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው 2% በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ/ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ተመላሽ የሚሆን (አጠቃላይ የሚወዳደሩበትን ዋጋ 2% ብር በቅ/ጽ/ ቤቱ ስም ማስያዝ አለባቸው። ለሎት 7. 8. 9. 10 በአጠቃላይ ለጥገና እቃዎች 3000 /ሶስት ሺህ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው አሸናፊ መረጣ የሚካሄደው ቅ/ጽ/ቤቱ በሚያዘጋጀው መስፈርት (የእቃ ጥራት መለኪያ) ፣ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ናሙና ወይም መ/ቤቱ በሚያዘጋጀው ናሙና እና በዋጋ መሆኑ ይታወቅ።
- የጨረታ ጊዜው የሚያበቃው 28/1/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- በቀን 28/1/2013 ዓ.ም ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ በግዥና ፋይናንስ ቢሮቁጥር 407 ውስጥ 4:30 በግልጽ ይከፈታል
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣ ጨረታውን ለማዛበት የሚሞክር ከጨረታው ወይም ይሆናል፤
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት እቃዎቹን መ/ቤቱ ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዞ ያቀርባል።
- ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፤
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከመሥሪያ ቤታችን ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፣ ከመስሪያ ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል
- በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ አካላት ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይገባቸዋል፡፡ የደብዳቤው ይዘትም ተጫራቹ በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ አቋርጦ ቢወጣ ለሚፈጠረው ክፍተት ዋስትና የሚሰጥ መሆን ይገባዋል፤
- መ/ቤቱ ጨረታውን በተከፈተ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ያሸናፊ ድርጅቶችን ዝርዝር ይፋ ያደርጋል፣
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ሆነ የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚፅፉት ማንኛውም አስተያየት