የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የገንዘብ ሚኒስቴር በጨረታ መለያ ቁጥር ገ/ሚ/ር/ግጨ/02/2012 Station Wagon Hard Top LWB Diesel (10-13 seats) መኪና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡
- በ2012 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና ከገቢ ግብር እዳ ነጻ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ዋናው መስሪያ ቤት የፋይናንስና ግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 36 የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 36 ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 36 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስቴር
የፋይናንስና ግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
ዋና መስሪያ ቤት
ቢሮ ቁጥር 36
የካቲት 12 አደባባይ ኪንግ ጆርጅ ጎዳና
ስልክ ቁጥር 251 011 157 43 19
ፖስታ ሣ.ቁ. 1905፣ 1037
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የገንዘብ ሚኒስቴር