በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የገንዘብ ሚኒስቴር በግዥ መለያ ቁጥር ገ/ሚ/ር/ግጨ/04/2012
የቢሮ ማሽኖች ሰርቪስና ጥገና አገልግሎት ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡
- በ2012 ዓ.ም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ፣ እና ከገቢ ግብር ዕዳ ነፃ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ዋና መሥሪያ ቤት የፋይናንስና ግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 36 ብር 100.00 በመክፈል መወሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 36 ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 36 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ዋና መሥሪያ ቤት
ቢሮ ቁጥር 36
6 ኪሎ የካቲት 12 አደባባይ ኪንግ ጆርጅ ጎዳና
ስልክ ቁጥር፡– 251 011 157 43 19
ፖስታ 1905፣1037
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስቴር
የፋይናንስና ግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት