የአዳራሽ እድሳት ማማከር ሥራ
የጨረታ ማስታወቂያ
የገነት ሆቴል አስተዳደር የዋናውን አዳራሽ፤ ምግብ ዝግጅት ክፍል እና ፋውንቴኑን እድሳት የማማከር ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና በቂ የማማከር ልምድ ያላችሁ የግንባታ ሥራ አማካሪ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
ተጫራቶች:-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የታደሰ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅቱ የሂሳብ ክፍል የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው እንደታወቀ የሚመለስ ብር 5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ “ ለገነት ሆቴል” ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዳችሁን የቴክኒክና የፋይናንሻል አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታው በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት በሆቴሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 6ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከናወን ይሆናል፡፡
- ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ጋር ውል መግባት ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ተገልፆ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀርቦ ውል ለማያስር የጨረታው አሸናፊ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡
- በጨረታው የሚሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ከታወቀበት ቀን በኋላ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ በስተግራ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0911250641/0913352447
የገነት ሆቴል አስተዳደር