የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር MOR/BA-02/2013
የገቢዎች ሚኒስቴር ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል:: ግዥዎችን የሚያመላክተው የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ ተመላክቷል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፡፡
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ መገናኛ አካባቢ ከሚገኘው የሚኒስቴር ዋ/መ/ቤት የግዥ ቡድን ህንፃ መሶስተኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 30 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ስልክ ቁጥር 0116-667-38-45/011-662-98-88
የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት