ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2013
1.በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት በ 2013 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቆች
- ልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መፅሀፍት
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ቋሚ ዕቃዎች
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ
- በዘርፉ የተሰማሩበት የንግድ ፍቃድ ያላችሁ
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) 10% ዋስትና ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 100 (አንድ መቶ ) የማይመለስ በመክፈል መግዛት የሚችል
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርበታል ::
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO ) ደግሞ የጨረታው ኮፒ ባለበት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባችኋል ::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ሰነዱ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርበታል ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀናት ከጠዋቱ፡ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ( ህጋዊ ወኪሎቻቸው ) በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል::
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን መሉ ለመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
አድራሻ:-አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ከንግድ ማተሚያ ጀርባ (ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አሮጌው ቄራ በሚወስደው መንገድ በሜሪስቶፕስ ትንሽ ገባ ብሎ)።
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት