የጨረታ ማስታወቂያ
የጅማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዘመን ከመንገድ ፈቃድ ጽ/ቤት ባገኘው የመንገድ ጥገና እና በከተማው የውስጥ ገቢ በጀት የከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን እንደሚከተለው በመከፋፈል፡፡
- Gravel Resurfacing /Rod Fund/Jimma/city/M-02/2013
- Gravel Resurfacing/Municipal/ lot 1 Jimma/City/M-03/2013
- Gravel Resurfacing/Municipal/ lot 2 Jimma/City/M-04/2013
- Gravel Resurfacing/ Municipal/ lot 3 Jimma/City/M-05/2013
ለመጠገን ይፈልጋል ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ስራ መስራት የሚችልን ድርጅት አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም፣ የሚከተሉትን መስፈርትና ሰነዶቹ ላይ የሚገኙትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ፍቃድ/ RC IV(4)/GC IV(4)/ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የግብር ከፋይና የተጨማሪ እሴት ታክስ (TIN & VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- በዘርፉ 2013 ዓ.ም. ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በ‘CPO’ ለእያንዳንዱ (ለአንዱ)ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታውን ሠድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመከፈል ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ የሥራ ፍቃድ በማቅረብ ከጅማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት (ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ) መግዛት ይችላሉ።
- 5 ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ መሠረት ዋጋ በመሙላት ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በመለየት በኤንቨሎፕ አሽገው ሦስቱን ደግመው በአንድ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው የሥራ ቀን 8:30 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- 6. ጨረታው በ21ኛው (21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን) ከቀኑ 8:30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 9:00 ሰዓት የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅማ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ለማስጠገን የፈለገውን መንገድ በሁሉም ቀበሌ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታን የሚገልጽ ማስረጃ ለጨረታው ከተዘጋጀው ሠነድ ጋር ማግኘት ይቻላል።
- ዝርዝር የመወዳደሪያ መስፈርት ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ የጅማ ከተማ ማዘጋጃቤት የመሰረተልማት ክፍል መጠየቅ ይቻላል። በተጨማሪም የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
አድራሻ፡–የጅማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡– 047119737/0471117083/0471115877/0471117049
ፋክስ 0471115856፡ የመሳ.ቁ.1597
የጅማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት