ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያ
- ሎት 2. የመኪና ጎማና ባትሪ
- ሎት 3. ሲሚንቶ
- ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 5.የውሃ ዕቃዎች
- ሎት 6.ፈርኒቸር
- ሎት 7. ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 8. የናፍጣ ትራንስፖርት ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት እና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
- የቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆነ።
- የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ሰለመሆናቸው ማረጋገጫቸውን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 30/ሰላሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለ30 ቀናት የሚቆይ እና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ–አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአየር ላይ ከ10/03/2013 እስከ 24/03/2013 ዓ/ም ድረስ ይውላል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ10/03/2013 ዓ/ም እስከ 24/03/2013 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 25/03/2013 ዓ/ም በዕለቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡15 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም።
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር/በሎት ድምር ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሲኖረው –አይፈቀድም ካለውም ፖራፍ ይደረግበት።
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸው ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ሁሉንም ዕቃዎችን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራንስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት ያለባቸው ሲሆን የጎማና ባትሪ ርክክብ ጎንደር ከተማ ላይ የሚደረግ ይሆናል።
- የናፍጣ መጓጓዣ የመጫኛና ማውረጃ በተቋሙ የሚሸፈን ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ 0582940023 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን
ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት