የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አፈተኢሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2013 ዓ.ም
- አላቂ የቢሮ እቃ ፣
- የትምህርት እቃ ፣
- የፅዳት እቃ ፣
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ግዢ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ
- ተጫራቾች አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የምዝገባ ፈቃድ ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 100/መቶ/መክፈል ይኖርባቸዋል
- ይህ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን መጥታችሁ ከቢሮ ቁጥር 24 መግዛት ትችላላችሁ።
- ጨረታው በተዘጋበት እለት /በ16ኛው የስራ ቀን ካለሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል።
- ት/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተነስቶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውንና ኦርጅናል የሚነበብ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00 (ሶስት ሺ) ጥሬ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር በት/ቤቱ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ት/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
የአፈተኢሳ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት