የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን 2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ፡ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ
- የጽህፈት መሣሪያና
- የፅዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስስዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡
- የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታቂያ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን የጽህፈት መሣሪያና የፅዳት እቃ ለማቅረብ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ማስረጃ፣ የዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ ለጽህፈት መሳሪያ ብር 15,140.33 አስራ አምስት ሺህ አንድ መቶ አርባ ብር ከሰላሳ ሶስት ሳንቲም/ ለፅዳት ዕቃ ብር 9,731.30 ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ አንድ ብር ከሰላሳ ሳንቲም/ በባንክ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ በሰንጠረዥ ውስጥ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 30 /2/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0251-1137-43/0251-11-7455 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ፖ.ሣ. ቁጥር 1453
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን