የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2013 ዓም በጀት ዓመት የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15/አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን የመኪና እቃ መለዋወጫ ለማቅረብ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ማስረጃ፣የዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ በሚጫረቱበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ በሰንጠረዥ ውስጥ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለትለየብቻ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 24/02/2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ይከፈታል።
- ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-35-37 በመደወል መረጃ ፖሣቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን