በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2013 በጀት ዓመት የዳቦ አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፣
- የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 150/አንድ መቶ ሃምሳ ብር በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣የሀገር ውስጥ ገቢ ድጋፍ ደብዳቤ ፣የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የምዝገባ ሰርተፊኬትና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ 50,000/ሃምሳ ሺ ብር/ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ እስከ Tahsas 1 2013 ዓ.ም. ከ4:00 ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው ሙግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተውተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 2/2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3.00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል::
- ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/025111-37-43 በመደወል መረጃ ፖሣ ቁጥር፡- 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን