የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2012ዓ.ም በጀት ዓመት ለፎረንሲክ መጠቀሚያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፓውደሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በውድድሩ ለመሳተፍ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚወዳደሩበትን እቃ ዋጋ 2% በባንክ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በማሸግና በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እስከ ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 19/2012 ዓም ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 025 111 74 55/025 111 3743
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት