የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት፡-
ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል በ15/አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስ ግዥና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን የደንብ ልብስ ለማቅረብ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ማስረጃ፣የዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ በሚወዳደርበት አልባሳት የጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እስከ 26/2/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 26/02/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0251-1137-43/0251-1174-55በመደወል መረጃ ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን