የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የድል በትግል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 :-የመምህራን ጋወን፣የሰራተኛ የደንብ ልብስ፣የስፖርት መምህራን ትጥቅ እና የደንብ ልብስ ስፌት ብር 7,722
- ሎት 2 :- አላቂ የቢሮ፣የትምህርት እቃዎች እና የላብራቶሪ እቃዎች ብር 7,077
- ሎት 3፡– ህትመት ብር 330
- ሎት 4 :- የጽዳት እቃዎች ብር 5,294
- ሎት 5 ፡–ቋሚ አላቂ እቃዎች ብር 880
በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች ፡
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- በዘመኑ የታደሰ የመንግስት ፈቃድ ያላቸው፤
- የእቃዎች ዋጋ 15% ቫት ተጨምሮ ይቅረብ፡ ባይቀርብ እንደተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50( ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተመረጡ እቃዎች እና ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ መታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር ) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን በቢሮ ቁጥር 01 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጭ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማምጣት አለባቸው፡፡ ት/ቤቱ ተጨማሪ በእቃዎች ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣ የመጨረሻ በ10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም በተገኘው ቢሮ ቁጥር 01 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የሚያስገቡበት ቦታ ቢሮ ቁጥር 01 የትምህርት ቤቱ ፅ/ቤት ሲሆን የሚከፈትበት ቦታ እዛው ቢሮ ይሆናል፡፡
አድራሻ፡– ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮ ሜዳ ከስፔን ኤምባሲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0111-22-25-38
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በጉለሌ ክ/ከተማ ት/መምሪያ
የድል በትግል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት