የጨረታ ማስታወቂያ
አራዳ ክ/ከተማ የዳግማዊ ምኒልክ የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/ደ የሥራ ሂደት ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ
- የደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅ
- የአላቂ የቢሮ እቃዎች የጽህፈት መሳሪያ ቋሚ ዕቃዎች (ፈርኒቸር እና ኮምፒዩተር ፕሪኒተር) እና
- የኮምፒዩተር ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና
- የመጋረጃ መስቀያ ብረት ከነማሰሪያው ፤
- የአጥር ሽቦ
በዚህ መሰረት፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ::
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡትን የወቅቱን የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ እና በአዲስ ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ያደረጉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከቢሮ ቁጥር 31 መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) እና የውል ማስከበሪያ ላሸነፈበት 10% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ(ሲፒኦ) ዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ት/ቤት በማለት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ ሰነዱ ላይ በመሙላት የግዥውን ዓይነት በኤንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ላይ ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል። ሆኖም ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ ነው በሳምፕል መቅረብ ለማይችሉ እቃዎች በፎቶ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አድራሻ 4ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ጎን ከቀድሞው አራዳ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-0111234219
አራዳ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት
የዳግማዊ ምኒልክ መሰናዶ ት/ቤት