ሕንፃ እና የዙሪያ አጥር ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለታርጫ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ሕንፃና የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቢሮና የዙሪያ አጥር ግንባታ ሥራ በ2012 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የታ/ከ/አስ/ር ማዘጋጃ ቤት የቢሮና የዙሪያ አጥር ግንባታ ሥራ
- ሎት 2. የታርጫ ከተማ አስ/ር ከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ሕንፃ ግንባታ ሥራ
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፤
- ደረጃቸው GC/BC 6 እና ከዚያ በላይ ሥራ ፈቃድ ያለው፣
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የሙያ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለዉ፤
- በዘመኑ የታደሰ የኮንስትራከሽን ሚኒስቴር የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
- የቫት/የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ከመንግሥት የግብር ዕዳ /Tax clearance/ ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከታርጫ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ቢሮ በመቅረብ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ/ ብር ለታ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ከፍሎ ሠነዱን ከታ/ከ/አስ/ር/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር አለባቸው፤
- ተጫራቾች ጨረታውን ሀ ቴክኒካል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ፣ እያንዳንዳቸው በሰም የታሸጉ እንዲሁም ሦስቱን የቴክኒካል ሰነዶች በአንድ የቴከንካል እናት ፖስታ በሰም የታሸጉ/ለፋይናንሻል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው በሰም የታሸጉ እንዲሁም ሦስቱም የፋይናንሻል ሰነዶች በአንድ የፋይናንሻል እናት ፖስታ በሰም የታሸጉ በማድረግ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት በሰም በማሸግ ታ/ከ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በታች በተገለጸው ቀንና ሰዓት መሠረት /Technical financial/ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርበታል። ኦርጅናሉ ላይ ኦርጂናል ኮፒዎች ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ አለባቸው።
- የጨረታ ቴክኒካል ዶክመንት ተገምግሞ መስፈርቱን ያሟሉ ተጫራች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋል፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /bid bond/ለእያንዳንቸው /50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም በሌሎች የግል ባንኮች የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። የሚያስይዙት CPO ወይም የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በተጨማሪም በሕንፃ ግንባታ ሥራዎች ላይ በቂ ልምድ ያላቸው እና ከዚህ በፊት ከ2009 ዓ.ም ወድህ ከሠሩባቸው ድርጅቶች ሥራውን አጠናቆ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ Performance letter/ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ካለፉበት ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራች የሚያቀርቡት ዋጋ ሲነበብ የነበረውና አርቲመትክ ቼክ ከተሠራ በኋላ ያለው ዋጋ ልዩነት ከ2% የበለጠ/ያነሰ ከሆነ ከጨረታው ዉድቅ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች ቅድመ ክፍያ የሚወስዱት በግዥ ህጉ መሰረት ተመጣጣኝ ዋስትና በማቅረብ ብቻ ነው።
- ሎት: 1 ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 እና ሎት 2 በ18ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳውሮ ዞን ተርጫ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግቢ ግዥ ን/አስ/ር ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፣ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታ መክፈት ሂደቱን እያስተጓጉልም፤
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡– 04 73450444/0917004606/0910978256 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡–መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደ/ብ/