ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የዳዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳዉ ስር ለሚገኘዉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች
- ለተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ አይነት የመኪና ጎማ እና ለሚትስ ቡሽ፤ ለቶዮታ፤ ለኒሳ የሚሆን የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን
መስፈርቶችም፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት (Tin No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና ከ200,000.00 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ የማይመለስ 50.00 ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ15 /በአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ገዝተው በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡40 የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ሆኖም የመከፈቻው ዕለት በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት በጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ 12 /ፐርሰንት/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ የተጫራቾች መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልክ ቁጥር. 33-554-17-92/0294 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዎች ያሸነፉትን ዕቃ ደዋ ጨፋ ወረዳ ገን/ኢኮ/ል/ጽ/ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ውል ካልገቡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሙሉ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ማወዳድራል ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የዳዋ ጨፋ
ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት