ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የዳባት ከተማ አስተዳደር ገ/አካ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የሴክተር መ/ቤቶች
- የፅህፈት መሳሪያ፣
- የደንብ ልብስ ፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የመኪና ዕቃዎች፣
- የፈርኒቸር እቃዎች ፣
- የፅዳት እቃዎች እና ሌሎች እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የጨረታ መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡- ተጫራቾች
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የ2013 የንግድ ፈቃድ ያደሱ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የንግድ ፍቃዱን በጀርባው ያለው የስራ ዘርፍ የሚገልፀውን ኮፒ አድርጎ ማያያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 – 5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር / ብቻ በመክፈል በዳባት ከተማ አስተዳደር ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢን ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ዋጋ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋና እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ዳባት ከተማ አስተዳደር ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 15 ቀናት ከ23/2/2013 እስከ 7/03/2013 ዓ/ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳባት ከተማ አስተዳደር ገ/አካ/ኢ/ ል//ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ 8/3/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን ዳባት ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዳባት ከተማ አስተዳደር ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581130456 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- 14. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት (በጥቅል) ድምር ነው::
የዳባት ከተማ አስተዳደር ገ/አካ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት