የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉአባቦራ ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም የበጀት ዘመን በሥሩ ላሉት መሥሪያ ቤቶች፣ ለሆስፒታል እና ለቴ/ሙያ እና ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የቢሮ ዕቃዎች ወይም ፈርኒቸሮችን
- የደንብ ልብሶች
- የግንባታ መሣሪያዎች
- የተለያዩ ጎማዎች
- የተለያዩ ህትመቶች
- የጋርሜንት ዕቃዎች ወይም ጨርቃ ጨርቆች
- የግብርና መሣሪያዎች
- የጸጉር መሥሪያ ዕቃዎች ወይም Hairdressing materials
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ::
- የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የሚያቀርቡት በጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከውድድር ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈፃፀም የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስተው ለተከታታይ የሥራ ቀን 15 ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከኢሉባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በመውሰድ ሁሉንም ሰነድ በሃምሳ ብር በመግዛት ዋጋውን ሞልተው ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ 27 ቀን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በ30 ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ30 ቀን በ 8፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዳሪሙ.ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታ ናቸው፡፡
- በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የዕቃው ብዛት ከውድድር በኋላ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በመሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ከተራ ቁጥር 1-12 በተጠቀሰው ያልተስማማ በጨረታው መሳተፍ የለበትም
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0474 44 0181/0262 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
Mobile No. 0987827860
በኢሉአባቦራ ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር
የዳሪሙ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽ/ቤት