Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle

የዲላ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ኮ/ል/ጽ/ቤት ለመንገድ ጥገና እና አዲስ መንገድ ግንባታ የሚያስፈልጉ ማሽኖች ዶዘር ማሽን፣ ግሬደር እና እስካቫተር እንዲሁም ሎደር ማሽን በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የዶዘር፣ ግሬደር እና እስካቫተር ማሽን የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2013

የዲላ ከተማ አስተዳደር /////ቤት 2013 በጀት ዓመት የማዘጋጃ ቤት ለሚያሰራቸው መሰረተ ልማት ለመንገድ ጥገና እና አዲስ መንገድ ግንባታ የሚያስፈልጉ ማሽኖች ዶዘር ማሽን፣ ግሬደር እና እስካቫተር እንዲሁም ሎደር ማሽን በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፤

ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች በኮንስትራክሽን ሥራ የማሽን ኪራይ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ሆነው፤ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤

 1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
 2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
 3. የንግድ ምዝገባ /ወረቀት ያላቸው
 4. የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው
 5. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 6. የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ cpo ማቅረብ የሚችሉ
 8. ማሽነሪ ነዳጅ፣ ቅባት፣ ግሪስ፣ የጥገና ወጭ እና የኦፕሬተር ወጪ እንዲሁም የማመላለሻ ሰርቪስ ጨምሮ መሸፈን የሚችል፡፡
 9. ማሽነሪ በከተማ ውስጥ አሰሪ /ቤት ወደሚፈልገው ስፍራ በሎቤድ ማመላለስ የሚችል፡፡
 10. ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም
 11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
 12.  ተጫራቾች አንድ ኦርጅናልና ፋይናንሻል 2 ኮፒ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናልና 2 ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ አሽጎ እናት ፖስታ በአንድ ላይ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ውሰጥ የጨረታ ሰነዱን ከዲላ ከተማ /ኢኮ///ቤት ከቢሮ ቁጥር 6 በመወሰድ መጫረት የምትችሉ፣ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ታሽጎ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤

*/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0463310107/3273/3133/ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት /ቤት