ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የዱራሜ ማረሚያ ተቋም በ2013 በጀት ዓመት የማገዶ እንጨትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፣
- ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እንዲሁም መንግሥት የሚፈለግበት ግብር እና ታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልፅ ለበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ወረቀት ሊያቀርብ የሚችል፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሲያቀርቡr የሚችሉ፡፡
- ድርጅቱ በራሱ ተሽከርከሪ በተባለው ቀንና ጊዜ ማረሚያ ተቋም ድረስ ሊያቀርብ የሚችል፡፡
- አሸናፊው በማንና ወም ዓይነት በቀረበው እንጨት የጥራት ችግር መኖሩ ከተረጋገጠ ለመለወጥ /ለመመለስ ፈቃደኛ የሚሆንና የሚስማማ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ ከታወቀ ባንክ ሕጋዊ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000,00 ከጨረታ ፖስታቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቦታ ዱራሜ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋይናንስ ቢሮ 19 በማቅረብ የማይመለስ የኢት ብር 100,00 በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡
- 9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ብር ከጠቅላላ አቅርቦት 10% በባንክ በተመሰከረለት (CPO) በቼክ በጥሬ ፐንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ30 ቀናት ነው፡፡
- አቅርቦት ከጥቅምት 1/2013 ዓም ጀምሮ ለ12 ወራት ለማቅረብ የሚስማማ መሆን አለበት፤
- አሸናፊው ለአቅርቦት ከላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት ጥቅምት 1ቀን 2013 ዓም እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለመቅረብ ሕጋዊ የውል ሰነድ የሚፈርም እና ባሸነፈው ነጠላ ዋጋ ለመቅረብ ፈቃደኛ የሚሆን፡፡
- እሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን የማገዶ እንጨት አጠቃልሎ ካስገባበት ቀን ጀምሮ የማገዶ እንጨቱን ጠቅላላ ዋጋ የክፍያ ጊዜ ሥራ ማስኬጃ እስኪመጣ ድረስ ለ15 የእፎይታ ጊዜ ሊሰጥ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ፡- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት የማገዶ እንጨት ከተዘረዘረው ልክ ነጠላ ዋጋ በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በ2/2/2013 ዓም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቶች (ሕጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በዱራሜ ማረሚያ ተቋም ውስጥ የሚከፈት መሆኑን ስንገልፅ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
- ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ማወዳደሪያ ፖስታ ሲታሸግ የእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማስረጃዎች አብረው መቅረብ እንዳለበት መዘንጋት የለበትም፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 0465541174/0912939051 ይደውሉ/በግ/ፋን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 19 በአካል ቀርበው ጠይቀው መረዳት ይቻላል፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ማረሚያ ቤቶች
አስ/ኮሚሽን የዱራሜ ማረሚያ ተቋም