የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች አገልግሎት የሚውል በድጋሚ መጠቀም የሚያስችል የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ Reusable Sanitary Pades/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የተቀበሉትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመከፈል ከቢሯችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5000 / አምስት ሺ ብር / በቢሯችን ስም በተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢድ ቦንድ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሯችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስት ማስገባት አለባቸው፡፡ ሳጥኑም በ15ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በቢሯችን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ የጨረታውን ማስከበሪያ ገንዘብ ላላሸነፉት ድርጅቶች ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት ወደ ቢሯችን መጥቶ አስፈላጊውን የጨረታ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈጽም ቀደም ሲል ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- በክልሉ ግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ ለአገር ውስጥ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አካላት በሚያቀርቡት ማስረጃ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ቢሯችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-3134
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት
የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች
ጉዳይ ቢሮ (ሀዋሳ)