የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠቅላላይ ዓቃቤ ህግ መ/ቤት የሚገለገልባቸው መኪናዎች ለአንድ ዓመት በሚቆይ ኮንትራት በሀዋሳ ከተማ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በትራንስፖርት ሚኒስቴር ወይም በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ ወይም በሲ/ብ/ክ/መ ትራንስፖርት ቢሮ ደረጃ-4 እና በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚትችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመስሪያ ቤቱ ግዢ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግንባር ቀርበው ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጥገና አገልግሎት በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማካተት የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነዳችሁ በሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ /ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ዓቃቤ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በዚሁ ዕለት/በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸግና በ4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በቂና ምቹ የጥገና አገልግሎት መስጫ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለጨረታ ኮሚቴዎች ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የጥገና አገልግሎት ማግኘት የሚፈልገው በሀዋሳ ከተማ ብቻ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር፡– 0462207327/ 046 2216200 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ግዥ/ፋ/ን/አስ/
ዳይሬክቶሬት