የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 011
ደቡብ ክልል ትም/ ቢሮ NCB
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ ለ2012 በጀት ዓመት በዩኒሴፍ በጀት ለተፋጠነ የትም/ቤት ዝግጁነት መርሀ ግብር ትግበራ የሚያገለግል ለትምህርት የሚሆኑ
- የጽህፈት መሳሪያዎችና
- የእግር ኳሶች ግዥ በሥራ መስኩ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
- በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የከፈሉበትንና የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ፣መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- የንግድ ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፊኬታቸውን የዘመኑን ያሳደሱበት እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ትምህርት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ለሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 30.00 /ሠላሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው:: ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 102 ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአንዱን ዋጋ ሞልተው ኦርጅናል እና ኮፒ ለይቶ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 102 ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 5,000.00 /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0462209637 መጠየቅ ይችላሉ::
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ትም/ቢሮ