የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 002
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መገሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለ2012 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የሚያገለግሉ የደንብ ልብስና ጫማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች
- በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝገቢ የሆኑ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመካተታቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች የዕቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ ብር 20.00/ሃያ ብር/ በመክፈል የንግድ ፍቃድ ኮፒ በመያዝ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁለቱም የሚወዳደሩ ከሆነ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) የደንብ ልብስ ብቻ ከሆነ 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር) ለጫማዎች ብቻ 2,000.00(ሁለት ሺህ ብር) CPO/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 6ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046 220 4750/046 221 1351/046-212 5541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት