ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የተሽከርካሪ ጥገና
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2013
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት የቀላል ተሽከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት ግዥ በመስኩ ከተሰማሩና በደረጃ አራት እና ከዚያ በላይ ከተመዘገቡ አገልግሎት ሰጪዎች የግዢ/ፋ/ን/አስ/ዳሬክቶሬት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት(በማቀፍ) ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከተጫራቾች መሟላት ያለበት:
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ግብር ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውና በተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ሰጪ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ አምስት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆያል ተጫራቾችም በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር ብቻ) ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000140245848 በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በመያዝ ደ/ክ/ከ/ል/ኮ/ቢሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 47 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) በመ/ቤቱ ስም ከታወቀ ባንክ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንት ወይም በጥሬ ገንዘብ በባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000140245848 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ወይም ሲፒኦውን ወይም ጋራቲውን ከቴክኒክ ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ፋይናንሽያል ዶክመንት ኦርጂናልና ኮፒ በተመሳሳይ ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነድ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ እስከ 45 ቀን ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ከሚመለከተው መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ (መምሪያ) በዘመኑ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ እና በዘመኑ የታደሰ የኢንሹራንስ መድን ዋስትና ሽፋን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ15ተኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል :: ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በሰንበት ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደተለየ ለጨረታ ማስከበሪያ የሺያጩን ጠቅላላ ዋጋ አሥር በመቶ ከታወቀ ባንክ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንት ወይም በጥሬ ገንዘብ በባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000140245848 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ወይም ሲፒኦውን ወይም ጋራንቲውን በማቅረብ ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ውል መግባት ይጠበቅባቸዋል
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ::
ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 046 220 5936 ፣ 046 220 9484
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ
ሃዋሳ