በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት ከህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በሶስት ሎት ማለትም በኤሌክትሮኒክስ፣ በፈርኒቸር እና በተለያዩ ህትመቶች ሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡
- ሎት -1 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት-2 ፈርኒቸር
- ሎት-3 የተለያዩ ህትመቶች
1.የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፈቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ በማድርግ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2.ከብር 200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) ከላይ የሚወዳደሩ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3.ተጫራቾች ለሎት1 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለሎት -2 ብር 4000.00 (አራት ሺህ ብር) እና ለሎት 3 ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
4.የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታተይ 15 ቀናት የማይመሰስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 209 በመግዛት በኤሌክትሮኒክስ ሎት ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦርጂናሉንና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5,በተለያዩ ህትመቶች እና በፈርኒቸር ሎቶች ፋይናሻል ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6.ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
7.ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ በስልክ ቁጥር 046-221-25-71 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሀዋሳ