የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብብ/ህ/ክ መንግሥት የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የተቀበሉትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል ከቢሮአችን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺ ብር) በቢሮአችን ስም በተዘጋጀና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ቢድ ቦንድ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አላስፈላጊውን መረጃ በማያያዝ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮአችን ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በቢሮአችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ ላላሸነፉት ድርጅቶች ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸለት ወደ ቢሮአችን መጥቶ አስፈላጊውን የጨረታ ውል መፈረም አለበት፡፡ ይህን ባይፈጽም ቀደም ሲል ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- በክልሉ ግዥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ ለአገር ውስጥ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አካላት በሚያቀርቡት ማስረጃ መሠረት ይስተናገዳሉ።
- ቢሮአችን ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-221-3134
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀዋሳ