የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣የጽዳት እቃዎች ከመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ
- የጽህፈት መሣሪያና ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች ከመደበኛ በጀት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በ2012 በጀት ዓመት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ዮግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin Number/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከብር 50000/ሀምሣ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆኑ የተጫራች እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።ተጫራቶች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው ስሎት በጥቅል ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በከፊል ወይም ቀንሶ መጫረት አይቻልም፡፡
- ለእያንዳንዱ እቃ የስፔስፊኬሽን ሙግለጫ መሞላት አለበት፤ ነገር ግን የስፔስፊኬሽን መግለጫው ያልተሞላበት እቃ ቢኖር ተጫራቹ ጽ/ቤቱ የሚፈልገውን ጥራት ያለው እቃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፣
- በጨረታው ሰነድ ላይ ማረጋገጫ ያልተቀመጠለት ስርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት አሻሚ የሆነ ፅሁፍ መኖር የለበትም
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ጋራንት በስማቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን እገልግሎት ጽ/ቤት በሚል አድራሻ በስማቸው ከኦርጅናል ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/ እገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሲጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/ አገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል:: ዕለቱ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።ሆኖም ተጫራቶች በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ ተሟልቶ ከተገኘ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል ፣
- አሸናፊው ተጫራች ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአሉት 5 የስራ ቀን በኋላ በአሉት 5 ተከታታይ ቀን ውስጥ መዋዋልና ስውሉ መሰረት እቃውን የማጓጓዣ ወጭን ችሎ በደ/ብ/ከ/አስ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቶች በሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ሊቀርብባቸው የሚችሉትን በትክክል ስለእቃው ሊገልፅ የሚችል ስፔስፊኬሽን በፅሁፍ ወይም በፎቶግራፍ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።በተጨማሪም የሚያስይዙት ዋስትና ጊዜ እቃው ተጠናቆ ርክከብ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ ለ1 ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው ፣
- በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ተጫራቶች ተጨማሪ ማብሪ ሪያ ከፈለጉ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0118906580/011 681 28 57 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት
ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት
የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር
ደጋፊ የስራ ሂደት