የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ቁጥር ደማ/01/2013
- የጨረታ ዙር 1ኛ
- የጨረታ ዓይነት መደበኛ
- የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ፣ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሀ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ለንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ – ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን:: በ10ኛው ቀን (መደበኛ ጨረታ) የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል ::
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ነው ::
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል ::
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን (መደበኛ ጨረታ) ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በጽ/ቤቱ ግቢ ተጫራቾች ወይም ይህ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ፡፡ 11ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት በአስር በመቶ ያላነሰ በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስልክ ቁጥር 0587713432 ወይም 0587714329 ደውሎ ማግኘት ይቻላል
የደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት