የደ/ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ፡-ሰርቨር ኮምፒዩተር፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ፣ ለሠራተኞች ሰርቪስ የሚሰጥ ደረጃ አንድ አውቶቡስ፣ ዩኒቨርሳል ሴንትሪፊውጅ፣ ኮምፓውንድ ማይክሮስኮፕ፣ ዩሪክ አሲድ፣ሆርሞን እና ካርዲያክ ማርከር እና ስናሳይዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የደ/ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ፡-ሰርቨር ኮምፒዩተር፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ፣ ለሠራተኞች ሰርቪስ የሚሰጥ ደረጃ አንድ አውቶቡስ፣ ዩኒቨርሳል ሴንትሪፊውጅ፣ ኮምፓውንድ ማይክሮስኮፕ፣ ዩሪክ አሲድ፣ሆርሞን እና ካርዲያክ ማርከር እና ስናሳይዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የደ/ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ፡-

 1. ሰርቨር ኮምፒዩተር፣ 
 2. የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ 
 3. ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን ምግብ፣ 
 4. ለሠራተኞች ሰርቪስ የሚሰጥ ደረጃ አንድ አውቶቡስ፣ 
 5. ዩኒቨርሳል ሴንትሪፊውጅ፣ 
 6. ኮምፓውንድ ማይክሮስኮፕ፣ 
 7. ዩሪክ አሲድ፣
 8. ሆርሞን እና ካርዲያክ ማርከር እና ስናሳይዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም፡-

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ 
 2. የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡፡ 
 3. የግዥ መጠን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 4. ተጫራቾች በጨረታለመሳተፍ ከላይ በተራቁጥር ከ-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቫትን ጨምሮ ጨረታ ማስከበሪያ 2000.00 ብር እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ውል ማስከበሪያ 10 % በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ድረስ ቀርበው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡ 
 6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። 
 8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/የስ/ሂደት ክፍል ይካሄዳል፡፡ 
 9. የተጫራቶች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡ 
 10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 (ሃያ ብር) በመከፈል ግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡ 
 11. አሸናፊው የተጫረተባቸው ንብረቶች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ከሆስፒታሉ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ 
 12. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 13. ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት 
 • በስልክ ቁጥር፡- 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 
 • ማሳሰቢያ፡- አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው በተነገረ በ10 ቀን ውስጥ ዕቃዎቹን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ዕቃዎቹ ገቢ የሚደረጉት ስባለሙያ ተረጋግጠው ዝርዝሩን ካሟሉ ብቻ ነው፤ ካልሆነ ግን ተመላሽ ይሆናሉ፡፡ 

በአ/ብ/ክ/መ ጤና ቢሮ 

የምስ/ጎ/መስ/ዞን ጤና መምሪያ 

የደ/ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል