የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ታቦር ከተማ አስ/ ከተማ ልማት ቤ/ኮ/አገልግሎት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ከሚያሠራቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውስጥ፡፡
- ቀበሌ 01 ከወርቄ ደመወዝ ቤት እስከ አስማማው አበበ ቤት 425 ሜትር ጠጠር መንገድ፣
- ቀበሌ 01 ከልጅቱ ማሪያም በቴሌ ታወር አድርጎ ጀበል መጨረሻ 680 ሜትር ጠጠር መንገድ፣
- ቀበሌ 04 ከቀጋ ውሃ ብሎኬት ሰፈር ወደ እርብ ተፈናቃይ ጠጠር መንገድ 400 ሜትር፣
- ቀበሌ 06 ከጌታቸው ፍቃዴ ቤት እስከ ሻንበል ጋሻው ቤት 652 ሜትር፣
- ቀበሌ 04 ከቀስተ ደመና ሆቴል ፊት በር ተነስቶ በእድር ቤት ታጥፎ እስከ ኮብል መንገድ ድረስ ጠጠር መንገድ 360 ሜትር፣
- ቀበሌ 04 ቀጋ ውሃ 12 ክፍል ሸድ ግንባታ ፣ ከደረጃ 8 እና በላይ የRC/GC ፈቃድ ካላቸው ተቋራጮች ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- ያቀረቡት ዋጋ ከ200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋና ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግንባታ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚችል ሲሆን የሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 300.00 ሦስት መቶ/ ወይንም ከቴ/መ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይቻላል ፣
- ስርዝ ድልዝ የሚያጋጥም ከሆነ ፓራፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፓራፍ ካልተደረገ ከውድድር ውጪ ይሆናል ፣
- ተጫራቾች ከሁለት ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም ከቴ/መ/ኢ/ጽ/ቤት ድጋፍ መያዝ አለባቸው ፣
- የግል ኮንትራክተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ ቢያንስ 10 በመቶ የመንግሥት ልማት ድርጅት ቢያንስ 15 በመቶ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች መስጠት አለባቸው ፣
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፣
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የእያንዳንዳችን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያልሞላ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤ/ኮ/ አገልግሎት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡-0581410091 /0584410033 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ በደ/ኅ/አስ/ዞን የደ/ታቦር ኮ/አስ/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት