Foodstuff and Drinks / Products and Services

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DBU05/12/2013

 

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 2013 እና 2014 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ልዩ ልዩ አቅርቦቶች

ማለትም፡-

  • ምድብ 1. ለተማሪዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ የዳቦ እርሾ፣ የዳቦ ፓውደር፣ ነጭ አዝሙድ፣ እርድ፣ በሶብላ፣ ዝንጅብል፣ ኮሰረት፣ ሮዝመሪ፣ ኮረሪማ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ የምግብ ጨው እና አቅርቦት በማዕቀፍ ውል ስምምነት 2 አመት አቅርቦት ግዥ
  • ምድብ 2. ለተማሪዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ብረታማ ስንዴ/የቅንጭ ስንዴ በማዕቀፍ ውል ስምምነት 2 አመት አቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታውለመሳተፍ፡-

ተጫራች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፡-

  • ለምድብ ) 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)
  • ለምድብ (2)50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባን በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥቃቅና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን ተጠቅሶ በአደራጃቸው /ቤት የበላይ ኃላፊ የተፈረመበት የዋስትና ደብዳቤ እንደ ምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በሚጫረቱበት ንግድ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየትኛውም ቅርንጫፍ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ በሂሳብ ቁጥር 1000025277515 ገቢ በማድረግ ዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ወይም 2 ስለትከከለኛነቱ ማህተም በማድረግ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-10 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::

4 ተጫራቾች በሁሉም ምድቦች የመወዳደሪያ ሀሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጂ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎኘ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር G-10 በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

5 ተጫራቾች በየምድብ 1እና 2 ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቀባቸውን ግብአቶች አስከ ጨረታ ማቅረቢያቀን ጠዋት 400 ሰዓት ድረስ ብቻ ዩኒቨርስቲው ግዥ ከፍል ኣቅርበው ለዩኒቨርስቲው   ባለሙያዎች በማስረከብ የርከከብ መተማመኛ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን ለመታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኘበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ ናሙና የተጠየቀባቸው ግብአቶች የናሙና ግምገማ ተደርጎ ናሙና የተመረጠባቸው ግብኣቶች የዋጋ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ18ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ በውጭና ህዝብ ግንኙነት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ናሙና ያልተመረጠላቸው ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱ ሳይከፈት ተመላሽ ይደረጋል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ (ትክክለኛው የመከፈቻ ቀኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል)፡፡ለምድብ 1 እና 2 ከተጠቀሱት አቅርቦቶች ከማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በሚቀርብ መረጃ መሰረት ዩኒቨርስቲው በየ3 ወሩ የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል።

7. ተጫራቾች ለውድድር በሚያቀርቡበት ናሙና ላይ የድርጅቱን ማንነት የሚገልጹ አርማ፤ ስም፣ ማህተምና መሰል ጉዳዮች መፃፍ የለባቸውም።ሁለቱም ምድቦች ላይ ለሚቀርቡ ናሙናዎች ተራቁጥሩን በእቃው ላይ ተጽፎበት መቅረብ አለበት፡፡

8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ ስራሳቸው ወጪ ዩኒቨርስቲው ድረስ ገቢ ማድረስ አለባቸው፡፡

9 ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉምየጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን::

10.ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስስኪቁጥሮች፡-011-895-97-56 ወይም 011-849 41-03 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት