የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DBU07/2013
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቤተሙከራ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፡
- ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በግዥ ኤጀንሲ ድረ–ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ወረቀትና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃና ከኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለምድብ1– ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ለምድብ-2 80,000 (ሰማኒያ ሺህ ብር)፣ ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ጋራንት፤ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ለዩኒቨርሲቲው በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ እንደምርጫቸው በአንዱ ለምድብ1 ከዋናው የቴክኒካል ሰነድ ጋር ለምድብ-2 ዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1000025277515 ገቢ በማድረግና በዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ወይም 2 ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማህተም በማስደረግ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር G-10 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ ለምድብ አንድ የዋጋና የቴክኒካል ሰነድ ዋናና ቅጅ (Original and copy) ለምድብ ሁለት የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ (Original and copy) ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር G-10 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የሁለቱም ምድቦች የጨረታ ሳጥን ታሽጎ የምድብ አንድ ጠዋት 4፡30 ላይ የቴክኒካል ሰነድ፣ የምድብ ሁለት የቀረቡ ናሙናዎች ግምገማ ከተከናወነ በኋላ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ18ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ላይ የዋጋ ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ከስነ–ምግባርና ፀረ–ሙስና እና ከውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬቶች ባለሙያዎች እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው የውጭና ህዝብ ግንኙነት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ዕለቱ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በበዓል ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሱት ቀናትና ሰዓት ይከፈታል/ትክክለኛውን የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ እንገልፃለን/። የምድብ ሁለት የቴክኒካል ሰነድ ግምገማ እንደተጠናቀቀ ውጤቱንና የዋጋ ሰነድ የሚከፈትበትን ቀን ለሁሉም ተጫራቾች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም::
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ዩኒቨርሲቲው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ድርጅቶች በስልክና በደብዳቤ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩት አንድ ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት የሚሰሩ ስልኮችን ማስቀመጥ አለባቸው።
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በኮፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0118959756/0118494103 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት