ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በፋብሪካው በምርት ሂደት ላይ የሚመረተው ለማገዶ እና ለተለያየ አገልግሎት የሚውል የግንድ ተረፈ ምርት (የግንድ ቅርፊትና መሰል እስክራፕስ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መረጃ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የተረፈ ምርቶቹን አይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታው መመሪያ ሰነድ ማግኘት ይቻላል ወይም በፋብሪካው ላይ በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፣ የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 50 ብር ከፍሎ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታው መመሪያ ላይ በተገለፀው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 02፡00 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይሆናል፤ ሆኖም ግን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4:30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ወይም በማግስቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቶቹ ከሥራ መስኩ ጋር ተያያዥነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የVAT እና TIN ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤ በውክልና የሚወዳደሩ አካላት ከፍትህ ወይም ከሰነዶች ማረጋገጫ ህጋዊ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116375273 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ
ኃ/የተ/የግ/ማህበር