የጨረታ ማስታወቂያ
ብግጨ 6/2013
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2013 የበጀት ዓመት ከመንግሥት በተመደበለት በጀት የምግብ ማከማቻ ቀሪ ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ሥራውን ለመሥራት የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለሥራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ ማቴሪያልና ማሽነሪዎችን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦ መሥራት የሚችል እና በደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የግንባታ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፣ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግሥት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሕንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪ ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሕንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሕንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቶች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል
- የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሽግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ — በስልክ ቁጥር 058-7166-91 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ