ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ብግጨ 13/2013
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለ 2013 በጀት አመት የዳቦ ዱቄት እና ለስላሳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴትታከስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ
- ሎት፡– የዳቦ ዱቄት ብር 80,000.00 /ሰማኒያ ሺህ ብር
- ሎት2፡– ለስላሳ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው፣
- 3 አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ 8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን ኣለበት፡፡
- 4 ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተ–ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ ለእያንዳንዱ ሎት በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
- 5 ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- 6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኘ ተጫራቶች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- 7. የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶከመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ ስታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን መሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- 8. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሰቢያ፡– የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 058-771-66-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ