የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 07/2013
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይገልጋል፡፡
ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎችም:
- የጽህፈት መሣሪያ
- ብትን ጨርቅ
- የወንድና የሴት ጫማ
- የተሰፋ ልብሶች
- የልብስ ስፌት
በመሆኑም በእያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ/ አስ/የስራ ሂደት በቅርብ የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስሂደት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም::
- በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል:: ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3-00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ/ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ መ/ቤቱ አይሸፍንም፡፡
- ተጫራቾች የሚፈጽሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ (መንገድ) ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ :- ደ/ማ/ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 771 68 40/ 058 771 10 58/ 058 771 15 20
ማሳሰቢያ፡
- ብትን ጨርቅ ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ናሙናውን እንድታዩ እናሳሰባለን::
- ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
- የደንብ ልብስ ስፌቱ የሚከናወነው በጽ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት