የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2013 በጀት አመት ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡
- 1ኛ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- 2ኛ/አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- 3ኛ/የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና
- 4ኛ/የጽዳት ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በጥቅል ወይም በተናጠል ዋጋ አወዳድሮ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
በዚህ መሰረት፡-
- 1) በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው
- 2) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- 3) የግዥ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- 4) ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- 5) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደብረብርሃን ክላስተር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ22/3/2013 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- 5) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የእያንዳንዱን ሎት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ስም ማሲያዝ ይኖርባቸዋል።
- 7 ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃ ክላስተር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 እስከ 15ኛው ቀን ማለትም በ6/4/ 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- 8) ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም 6/4/2013 ዓ.ም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚህ እለት 4፡30 ይከፈታል።
- 9) ሆኖም የጨረታ መክፈቻው እለት የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- 10) ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ በሌላኛው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የለበትም።
- 11) የጨረታ ግምገማው በጥቅል ወይም በተናጠል ድምር የሚካሄድ በመሆኑ ተጫራቾች የሁሉም ዕቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው የዕቃ ጥራት ደረጃ ናሙና እና እስፔስፊኬሽን መሰረት ሲሆን የቀረቡትም ናሙናዎች የኮፒማሽን ቀለም የማህተም ቀለም እና የፕሪንተር ቀለም ናቸው። በተቻለ መጠን ዋጋ ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል።
- 12) በጨረታው ለመሳተፍ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በአካል ቢሮ ቁጥር 07 ወይም 011 637 66 58/59 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
- 13) መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ: ኣድራሻ ሼል /ኦሬንታል/ ካፌ ፊት ለፊት አቶ ብሩክ ነጋሽ ህንፃ ላይ፡
የደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ
ማዕከል ግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን
ደብረብርሃን