ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን፡
- የመኪና መለዋወጫ እቃ ፤
- የመኪና ጎማ
- የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin number/ ያላቸው፤
- የግዥ መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- . ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፤
- የመኪና መለዋወጫ እቃ የመኪና ጎማ እና የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ህትመት አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ብ/ከ/አስ//ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ቢሮቁጥር2በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16/ አስራ ስድስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚህም ሰዓት ይታሸጋል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ታዛቢዎችና የውስጥ ኦዲተሮች በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሠረት በጥቅል/ በሎት ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ደ/የስራ ሂደት መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፤
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ደ/ብ/ከ/አስ/ገን/ኢኮ/ት/ጽ/ ቤት በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 118909064/ 0116814788 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ብርሃን አስ/ገንዘብ ካ/ኢኮ ትብብር ጽ/ቤት
የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር